በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ የፀጥታ ሃይሎች የተያዙ 34 ሰዎች የገቡበት አልታወቅም


ባለፈው ሳምንታት ተሰውረ ቆይቶ ሬሳቸው የተገኘው ሦስት ሰዎች
ባለፈው ሳምንታት ተሰውረ ቆይቶ ሬሳቸው የተገኘው ሦስት ሰዎች

ሁማን ራይትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብቶች ተማጓች ድርጅት የኬንያ የፀጥታ ሀይሎች ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ናይሮቢንና ሰሜን ምስራቅ ኬንያን ከአል ሸባብ ደጋፊዎች ለማፅዳት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰዎች የገቡበት እንዳይታወቅ አድረገዋል ሲል ከሷል።

ሁማን ራይት ዋች የኬንያ መንግስት በአሸባሪነት የሚጠረጠሩ ሰዎችን ለመንቀል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አቁሞ በተግባሩ ላይ ምርመራ እንዲያካሄድ ጥሪ ማቅረቡን ታውቋል።

“ሞትና መሰወር” በሚል ርእስ የወጣ ዘገባ ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ 34 የሚሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ የፀጥታ ሀይሎች እጅ ላይ የወደቁ ሰዎች የገቡበት አልታወቀም ይላል።

የሁማን ራይትስ ዋች ዋና ስራ አስኪያጅ ኬኔት ሮት የተለያዩ የሀገሪቱ የጸጥታ አገልግሎቶች ወታደራዊ ሃይሉም ጭምር በሰብአዊ መብት ረጋጣው ተግባር ተሳትፈዋል ብለዋል።

ሰዎች ከተያዙ በኋላ አንዳንዶቹ በሰሜን ምስራቅና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ሚገኙ ማጎርያ ሰፈሮች እንደሚወሰዱ መርማሪዎቹ ለማወቅ ችለዋል።

ሁማን ራይትስ ዋችና ሃላፊው እያንዳንዱ በሀገሪቱ ያለ የጸጥታ ክፍል በጸረ ሽብሩ እንቅስቃሴ ይሳተፋል ይላሉ።

አራት ኬንያውያን ፖሊሶች ከሦስት ሰዎች ሞት ጋር በተያያዘ በያዝነው ሳምንት በግድያ ወንጀል ተከሰዋል። ሦስቱ ሰዎች በፖሊስ ተይዘው ነበር ከተባለ ጥቂት ቀናት በኋላ አስከሬናቸው ናይሮቢ አጠገብ በሚገኝ ወንዝ ላይ ተገኝቷል።

ነፃው የፖሊሶች ተቆጣጣሪ አካል ፖሊሶችን የመመርመር ስልጣን አለው። ሌሎች የፀጥታ ክፍሎችን ግን ሊመረምር አይችልም።

መንግስት ወታደራዊ ሃይሉም ጭምር ይፈጽማቸዋል የተባሉትን የሰብአዊ መብት ረገጣዎችን የሚመረምር ኮሚሽን እንዲሰይም ሁማን ራይትስ ዋች ጥሪ አቅርቧል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በኬንያ የፀጥታ ሃይሎች የተያዙ 34 ሰዎች የገቡበት አልታወቅም
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG