በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬኒያው ሄሊኮፕተር አደጋ ከሞቱት መካከል አንዱ የመከላከያ ኃይሎች አዛዡ መሆናቸው ተገለጠ


ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ እና የኬንያ መከላከያ ኃይል አዛዥ ጀነራል ፍራንሲስ ኦጎላ
ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ እና የኬንያ መከላከያ ኃይል አዛዥ ጀነራል ፍራንሲስ ኦጎላ

ትናንት ሐሙስ ኬኒያ ውስጥ በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ከሞቱት ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የመከላከያ ኃይሎቹ አዛዥ መሆናቸውን የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ ተናገሩ።

ሩቶ ስለአደጋው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ "እጅግ አሳዛኝ በሆነው በዚህ አደጋ አገራችን እጅግ ጀግና ከሆኑት ጄኔራሎቿ አንዱን በሞት ተነጥቃለች። በጄኔራል ፍራንሲስ ኦጎላ ሞት እጅግ አዝኛለሁ" ብለዋል።

ሄሊኮፕተሩ ጄኔራሉን እና ሌሎች 11 ወታደራዊ አባላትን አሳፍሮ እንደተነሳ ብዙም ሳይቆይ በምዕራባዊ ኬንያዋ ሪፍት ቫሊ ክፍለ ግዛት ውስጥ ወድቆ ቃጠሎ መነሳቱን ዘገባዎች አመልክተዋል። ከአደጋው የተረፉ ሁለት ሰዎች ሆስፒታል ህክክምና ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል በተዋጊ አውሮፕላን አብራሪነት የሰለጠኑት ጄኔራል ኦጎላ የኬኒያ የአየር ኃይል አብራሪዎች አሰልጣኝ የነበሩ ሲሆን ፕሬዚደንት ሩቶ የጦር ኃይል አዛዥ እንዲሆኑ የሾሟቸው እአአ በዚህ ዓመት መሆኑ ተመልክቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቫን ለኬኒያ ፕሬዚደንት እና ሕዝብ ስለደረሰው አደጋ ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ጄክ ሰለቫን ባወጡት መግለጫ ጄኒራል ፍራንሲስ እጎላ ለአርባ ዓመታት በዘለቀው አገልግሎታቸው በኬኒያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት ትልቅ ስፍራ ያላቸው አጋር ነበሩ ብለው የሀገራቸውን እና የሁላችንንም ደህንነት ለመጠበቅ ራሳቸውን የሰጡ ብለዋቸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG