በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊ ኬንያ ገጠራማ አካባቢዎች ሁከት ተባብሷል


ፎቶ ፋይል፡- ባራጎይ ኬንያ
ፎቶ ፋይል፡- ባራጎይ ኬንያ

በማዕከላዊ ኬንያ ገጠራማ አካባቢዎች ባለፉት ወራት ሁከቱ ተባብሶ መቆየቱ ተገለጠ።

በማዕከላዊ ኬንያ ገጠራማ አካባቢዎች ባለፉት ወራት ሁከቱ ተባብሶ መቆየቱ ተገለጠ።

ይህ የሆነው ከሰሚኑ የሀገሪቱ ክፍል የታጠቁ አርብቶ አደሮች ብዛት ያላቸው የቀንድ ከብቶች ፍየሎችና በጎቻቸውን ወደግል የግጦሽ መሬት በመንዳታቸው መሆኑ ተገልጧል።

በግጭቱ የሰውና የዱር አራዊት ህይወት አልፉል።

ድርቁ እያተባባሰ ባለበት ወቅት አንዳንዶቹ የፖለቲካ መሪዎች ህዝቡን ከብቶቻችሁን ሣርና ውሃ ወዳለበት የፈለጋችሁበት ቦታ ይዛችሁ መሄድ ትችላላችሁ ብለው መቀስቀሳቸው ግጭቱን ለማብረድ እንዳልረዳ ተጠቁሟል።

የኬንያ የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ምዌንዳ ኢንጆካ ሲናገሩ በማዕከላዊ ግዛቶች የፀጥታ ጥበቃው እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ገልፀዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG