በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ወደ ሄይቲ የፀጥታ ኃይል መላኩን እንደምትገፋበት አስታወቀች


የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ
የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ

በወሮበሎች ትርምስ ውስጥ ወዳለችው ሄይቲ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪነት የፀጥታ ኃይል በመላኩ እንደምትገፋበት የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ዛሬ ዓርብ አስታውቀዋል።

የኬንያ መንግስት 1ሺሕ የሚሆን የፖሊስ ኃይል ወደ ሄይቲ በሣምንታት ውስጥ ለመላክ ቢወስንም፣ በሃገሪቱ የሚገኙ የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውስድ ለማስቆም በመጣር ላይ ናቸው። ባለፈው ጥር አንድ ፍርድ ቤት ዕቅዱ ኢ-ሕገ መንግስታዊና ሕገ ወጥ በማለት የበየነ ሲሆን፣ መንግስት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ችላ ብሏል በሚል ተቃዋሚዎች አዲስ ክስ በከፍተና ፍ/ቤት ከፍተዋል።

ከፍተኛው ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ ከአስር ቀናት በኋላ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል።

የፀጥታ ልዑኩ ከሶስት ሣምንታት በኋላ ወደ ሄይቲ እንደሚላክ ፕሬዝደንት ሩቶ ባለፈው ሣምንት ዋሽንግተንን በጎበኙበት ወቅት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

አንድ የቃኝ ቡድን ወደ ሄይቲ ልከው፣ በመሬት ላይ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ ሪፖርት መቀበላቸውን ሩቶ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG