በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ መንግስት የፖሊስ ኃይል ወደ ሄይቲ ለመላክ የያዘውን ዕቅድ ፍ/ቤት አገደ


የኬንያ መንግስት 1 ሺሕ የሚሆን የፖሊስ ኃይል ወደ ሄይቲ ለመላክ የያዘውን ዕቅድ አንድ በናይሮቢ የሚገኝ ፍ/ቤት ለግዜው አግዶታል።

ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት የወሰዱት ሶስት ግለሰቦች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የሆኑት የተቃዋሚው ፖለቲከኛ ኢኩሮ አውኮት ለቪኦኤ ሲናገሩ፣ ፖሊስን ወደ ሄይቲ ለመላክ መታቀዱ ኢ-ሕገመንግስታዊ ነው ብለዋል።

መንግስት ሌላ የመከራከሪያ ዘዴ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው። በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት ከ12 ቀናት በኋላ በሚኖረው ቀጠሮ ጉዳዩ እስኪታይ ድረስ፣ ወደ ሄይቲም ሆነ ወደ ሌላ ሀገር መንግስት ፖሊስ እንዳይልክ ታግዷል።

ኬንያ ወደ ሄይቲ የሚላክን ከሀገራት የተውጣጣ ሃይል እንድትመራ የተመድ ፀጥታው ም/ቤት ባለፈው ሳምንት ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

መንግስት በጉዳዩ ላይ ክርክሩን እንደሚያቀርብ፣ እንዲሁም ለፍ/ቤቱ ውሳኔ ተገዢ እንደሚሆን አንድ የመንግስት ተወካይ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG