በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይሮቢ በተነሳ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሞቱ 222 ቆሰሉ


የደረሰውን የጋዝ ፍንዳታ ተከትሎ በስፍራው የነበሩ ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው ሲሮጡ ኢምባካሲ፣ ናይሮቢ፤ ኬንያ እአአ የካቲት 2/2/2023
የደረሰውን የጋዝ ፍንዳታ ተከትሎ በስፍራው የነበሩ ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው ሲሮጡ ኢምባካሲ፣ ናይሮቢ፤ ኬንያ እአአ የካቲት 2/2/2023

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ኢምባካሲ በሚባለው ሰፈር ትናንት ሐሙስ ማምሻውን የደረሰውን የጋዝ ፍንዳታ ተከትሎ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 222 ያህሉ ደግሞ ቆስለዋል።

ጋዝ ከተጫነ የጭነት መኪና ላይ የተከሰተው ፍንዳታን ተከትሎ የተፈጠረው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በአካባቢው ወደሚገኙ ተሽከርካሪዎች፣ የንግድ ንብረቶች እና የመኖሪያ ሕንፃዎች ላይ በፍጥነት መዛመቱም ተነግሯል፡፡

የመንግስት ቃል አቀባይ አይዛክ ምዋውራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንዳስታወቁት እየተካሄደ ያለውን የነፍስ አድን እና የእርዳታ ስራዎችን የሚያስተባብር የእዝ ማእከል መቋቋሙን ገልጸው ህብረተሰቡ ለአደጋው ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል ብለዋል።

ክስተቱ ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ከጋዝ ማከማቻ እና መጓጓዣ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አደጋዎች የደህንነት ስጋቶችን በመፍጠሩ ትኩረት እየሳበ መምጣቱ ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG