በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ሰሜን ምሥራቅ ግዛት በደረሰ ፍንዳታ በርካቶች ቆሰሉ


የሶማሊያ አዋሳኝ በሆነችው ማንዴራ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ ሦስት ፖሊሶችን ጨምሮ በርካቶች ቆስለዋል፡፡
የሶማሊያ አዋሳኝ በሆነችው ማንዴራ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ ሦስት ፖሊሶችን ጨምሮ በርካቶች ቆስለዋል፡፡

በኬንያ ሰሜን ምስራቅ ግዛት ባለ ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ አንድ ትንሽ ሆቴል ትናንት ሰኞ በደረሰ ፍንዳታ ሦስት ፖሊሶችን ጨምሮ በርካቶች ቆስለዋል ሲሉ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የሶማሊያ አዋሳኝ በሆነችው ማንዴራ ከተማ ሆቴሉ ውስጥ የተቀበረው ፈንጂ የፈነዳው ሰዎች ቁርስ ለመብላት በተሰባሰቡት ወቅት መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

መርማሪዎች ለጥቃቱ ፅንፈኛ ታጣቂውን ቡድን አልሸባብን ተጠያቂ አድርገዋል። ቡድኑ ለፍንዳታው ሃላፊነቱን ያልወሰደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኬንያ እና በጎረቤት ሶማሊያ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል።

የኬንያ መንግሥት ባለፈው ዓመት ከሶማሊያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር እንደገና ለመክፈት ማቀዱን ቢያስታውቅም ፅንፈኞች በሚያደርሷቸው ጥቃቶች ምክንያት ለሌላ ጊዜ አስተላልፏል።

የቅርቡ ጊዜ ጥቃት የተፈጸመው ባለፈው እሁድ በኬንያ የባህር ዳርቻ ላሙ ወረዳ ውስጥ ሁለት ተጠባባቂ ፖሊሶች የተገደሉበትን ሌላ ጥቃት ተከትሎ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG