በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ እና የአውሮፓ ኅብረት የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ


የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሰላ ቮን ደር ላየን፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሰላ ቮን ደር ላየን፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ

ኬንያ እና የአውሮፓ ኅብረት፣ በሁለቱ ወገኖች በኩል የሸቀጦች ልውውጥን ለማሳለጥ ለረጅም ግዜ ድርድር ሲያደርጉበት የሰነበቱትን የንግድ ስምምነት ዛሬ ሰኞ ተፈራርመዋል። ኅብረቱ ከአፍሪካ ጋር የጠነከረ የኢኮኖሚ ግንኙነት መሻቱን የሚያመላክት ነው ተብሏል።

ስምምነቱ፤ ኬንያ ከቀረጥ እና ከኮታ ነፃ በሆነ መንገድ የውጪ ንግዷ ዋና መዳረሻ ወደሆነው አውሮፓ ኅብረት ሸቀጥ እንድታስገባ ያስችላታል። ወደ ኬንያ የሚገቡ የአውሮፓ ሸቀጦች ደግሞ ቀረጣቸው ቀስ በቀስ እየቀነሰ እንደሚሄድ ታውቋል።

ስምምነቱ፤ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ መካከል ከእ.አ.አ 2016 ወዲህ የተደረገ ትልቅ የንግድ ስምምነት ነው ተብሏል። ቻይና በመላ አህጉሪቱ የመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ማፍሰሷን ተከትሎ የመጣ እንደሆነ ተመልክቷል።

ሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ስምምነቱን እንዲቀላቀሉ የጠየቁት የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሰላ ቮን ደር ላየን፣ ከአፍሪካ ጋር የንግድ እና የኢኮኖሚ ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ እንደመጡ ተናግረዋል።

ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን የአውሮፓ ኅብረት እና የኬንያ ፓርላማ ማጽደቅ እንደሚጠበቅባቸው የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG