በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ስደተኞች ሕይወት ዛሬም እንደከፋ ነው


ናይሮቢ
ናይሮቢ

ዩኤንኤችሲአር የሶማሌ ስደተኞች በፍቃዳቸው እንዲመለሱ ይፈልጋል፡፡

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች የታሠሩበት የናይሮቢው ካሳራኒ ስታዲየም
በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች የታሠሩበት የናይሮቢው ካሳራኒ ስታዲየም
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኬንያ ውስጥ በስደተኞች ላይ የተጀመረው አፈሣና እየተወሰደ ያለው እርምጃ በዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት የተከሰሱት የሃገሪቱ መሪዎች በዙሪያቸው ያለውን ሁኔታ ለማድበስበስ አስበው የፈጠሩት ነው ሲሉ ስደተኞቹ እየወቀሱ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ ከመንግሥት ጋር እየሠራ መሆኑን ናይሮቢ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ለቪኦኤ ገልጿል፡፡

ላለፉት ሃያ ዓመታት ናይሮቢ የኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ እንደገለፁት ከዚህ በፊትም በተፈጠሩ ተመሣሣይ ችግሮች ምክንያት ከመንግሥቱ ጋር እስከመካሰስ የደረሱበትና ፍርድ ቤት ለስደተኛው የፈረደበት ጊዜ እንደነበረ አስታውሰው በተሰጣቸው ፍቃድም እየሠሩና ለመንግሥት ግብር እየከፈሉ መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ መንግሥት የፍርድ ቤቱን ውሣኔና ትዕዛዝ እየጣሰ የራሱን ደንቦች ሲያወጣና እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱን ስደተኛው አመልክተው የአሁኑንና እስከዛሬም የቀጠለውን አፈሣና እሥራት በፀጥታ ሰበብ አድርጎ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

የኬንያ መሪዎች ይህንን እርምጃ እየወሰዱ ያሉት በዓለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በተመሠረተባቸው ክሥ ምክንያት የተጣለባቸውን ትኩረት ለማራቅ ብቻ ሣይሆን በአንዳንድ የፀጥታ ኃይሉ አባላትና ባለሥልጣናት ጥቅምና ገንዘብ ፍላጎትም ጭምር መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኬንያ መንግሥትና ዩኤንኤችሲአር የደረሱበት መፍትኄ የሶማሊያ ስደተኞችን በፍቃዳቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መሆኑን ናይሮቢ የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃልአቀባይ ኢማኑኤል ኝያቤራ አስረድተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG