በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይሮቢ የኢትዮጵያ ስደተኞች የመሰብሰብ መብት ተከለከልን አሉ


በናይሮቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ስደተኞች
በናይሮቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ስደተኞች

በናይሮቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሠብ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግሥት የኬንያ ፖሊስን ተጠቅሞ በስደተኛው ላይ ጫና ማድረጉን አላቆመም በማለት ተናገሩ።

በናይሮቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሠብ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግሥት የኬንያ ፖሊስን ተጠቅሞ በስደተኛው ላይ ጫና ማድረጉን አላቆመም በማለት ተናገሩ። በዚህም የተነሳ በየዓመቱ በኬንያ ናይሮቢ “ሲት ፓርክ” ይከበር የነበረው የእሬቻ በዓል የኬንያ ፖሊስ ፍቃድ በመከልከሉ በናይሮቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሠብ በዓሉን ሳያከብሩ ቀርተዋል።

በናይሮቢ የኦሮሞ ስደተኞች ማኅበረሠብ ፀኃፊ አቶ ፍቃዱ ድርባ ለአሜርካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ማኅበራችን በኬንያ በሕጋዊነት ተመዝግቦ ያለ ማኅበር ቢሆንም የኬንያ ፖሊስ የማኅበሩ ኮሚቴ እንዳይገናኝ ፍቃድ በመከልከሉ በኬንያ ያሉትን ስደተኞች መርዳት አልቻልንም ብለዋል።

በኬንያ የኢትዮጵያ ቆንሲላ ጽሕፈት ቤት የፖብሊክ ዲፕሎማሲ እና ሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ አቶ ሀብታሙ ባዬ

“ኢምባሲው የኬንያ ፀጥታ አካላትን የሚያዝበት ሁኔታ የለም” በማለት የቀረበውን ሰሞታ አጣጥለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በናይሮቢ የኢትዮጵያ ስደተኞች የመሰብሰብ መብት ተከለከልን አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG