በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ምርጫ በታቀደው መሠረት ይካሄዳል

የኬንያው ፕሬዚዳንታዊ የማጣርያ ምርጫ በታቀደው መሠረት እንደሚካሄድ ታውቋል። የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማጣርያ ምርጫውን ጊዜ ስለማስተላለፍ ጉዳይ ለመስማት ባለመቻሉ ነው በቀጠሮው መሰረት እንዲፀና የተደረገው።

የኬንያው ፕሬዚዳንታዊ የማጣርያ ምርጫ በታቀደው መሠረት እንደሚካሄድ ታውቋል። የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማጣርያ ምርጫውን ጊዜ ስለማስተላለፍ ጉዳይ ለመስማት ባለመቻሉ ነው በቀጠሮው መሰረት እንዲፀና የተደረገው።

“የሚመለከታቸው ባለሥልጣኖችና የፀጥታ አገልግሎቶች ለዚህ ኮሚሽን በሰጡት ማረጋገጫ መሰረት ምርጫው በታቀደው መሰረት ነገ ይካሄዳል ሲሉ የነፃው የምርጫና የድንበር ጉዳይ ኮሚሽን ኃላፊ ዋፉላ ቸቡካቲ አስታውቀዋል።

ዋናው ዳኛ ዴቪድ ማራጋ በገለጹት መሰረት የምርጫውን ጊዜ ስለማስተላለፍ ድምፅ መስጠት ያለባቸው ሰባት የፍርድ ቤቱ ዳኞች ሆነው ሳለ የተገኙት ሁለት ብቻ በመሆናቸው ድምፅ ለመስጠት አልተቻለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG