በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ምርጫ ውጤት ተገለፀ


ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

የኬንያ ምርጫ ቦርድ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ያጣጣሉትን ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ። በምርጫው ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ደምፅ አግኝተው ማሸነፋቸውን የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር ዋፉላ ቸቡካቲ ገልፀዋል።

የኬንያ ምርጫ ቦርድ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ያጣጣሉትን ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ። በምርጫዉ ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ደምፅ አግኝተው ማሸነፋቸውን የኬንያ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር ዋፉላ ቸቡካቲ ገልፀዋል።

ምርጫዉ በፀጥታ ችግር በሙሉ የሀገሪቱ ግዛት ያልተደረገ ሲሆን የምርጫ ቦርድ ምክትል ኮሚሽነር ኮንሶላታ እንጋታ በኬንያ አራት ግዛቶች ምርጫው ባይደረግም የሀገሪቱ የምርጫ ሕግ መሠረት የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤቱን ይፋ ማድረጉን ገልፀዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ የነበሩት ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ

“ምርጫው ተቀባይነት የሌለው ምርጫ ነው" ሲሉ የኬንያታን ድጋሚ መመረጥ አጣጥለዋል።

ለመምረጥ ከተመዘገቡት 19 ሚሊዮን በላይ ኬንያዊያን ወደ 7 ሚሊዮን ብቻ ናቸው በድጋሚ በተደረገው የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ የተሳተፉት። በዚህ ምርጫ ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ድምፅ አግኝተዉ ማሸነፈቸውን የኬንያ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኬንያ ምርጫ ውጤት ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:46 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG