ኬንያ ውስጥ ሰባት የሐኪሞች ማኅበር ባለሥልጣናት ለአንድ ወር በእስር እንደሚቆዩ ተገለፀ።
ሐኪሞቹ ለእስር የተዳረጉት፣ የአገሪቱን የጤና አገልግሎት ከሁለት ወር በላይ አሰናክሎ ያቆየው የሥራ ማቆም ዓድማ እንዲያበቃ ባለማድረጋቸው እንደሆነም ተገልጿል።
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትና በሀኪሞቹ ማሕበር ጠበቃ መካከል ከሁለት ሰዓታት በላይ የተካሄደውን ውይይት ያዳመጡት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሄለን ዋሲዋ አንድ ወር እስራት በይነውባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ