በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ የአምልኮ ቡድን መሪው ፍርድ ቤት ቀረበ


“በሰማይ ቤት ክርስቶስን እንድታገኙ ተራቡ” በሚል ከ400 በላይ ሰዎች ሕይወት እንዲጠፋ አድርጓል የተባለው ኬንያዊና ግብረ አበሮቹ የፍርድ ሂደት ዛሬ ቀጥሏል።

ራሱን ፓስተር ብሎ የሚጠራው ፖል ማኬንዚ እና ሌሎችም በርካታ ተጠርጣሪዎች ለቀረቡባቸው ክሶች ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ባለፈው ጥር ለፍርድ ቤት አስታውቀው ነበር።

ማኬንዚ 93 ከሚሆኑ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋራ ሞምባሳ በሚገኝ ፍርድ ቤት ዛሬ መቅረቡ ታውቋል።

የአምልኮ ቡድን መሪው ማኬንዚ፣ ተከታዮቹን “ክርስቶስን እንድታገኙ ተራቡ” ብሉ በማነሳሳቱ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል የሚል ክስ ቀርቦበታል። አስከሬናቸው ለወራት ከአንድ ጫቃ ውስጥ እየተቆፈረ ሲወጣ እንደነበር ይታወሳል። በፍለጋው 448 አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በረሃብ እንደሞቱ፣ ከአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ የውስጥ ሰውነት ክፍላቸው መወሰዱ እንደታወቀ የተደረገው ምርመራ አመልክቷል ተብሏል።

የማኬንዚን ባለቤትን ጨምሮ 95 ሰዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።

በተከሳሾቹ ላይ ለመመስከር 420 ሰዎች እንደተዘጋጁ ከሳሽ አቃቤ ሕግ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG