በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ራሳቸውን በረኀብ የገደሉ ሰዎች አስከሬን እየተመረመረ ነው


በኬንያ ራሳቸውን በረኀብ የገደሉ ሰዎች አስከሬን እየተመረመረ ነው
በኬንያ ራሳቸውን በረኀብ የገደሉ ሰዎች አስከሬን እየተመረመረ ነው

በኬንያ፣ “ኢየሱስን እንድታገኙ ተራቡ” ተብሎ በቤተ ክርስቲያን መሪያቸው ከተነገራቸው በኋላ፣ ከምግብ ታቅበውና ራሳቸውን ለረኀብ ዳርገው የሞቱ ከመቶ በላይ ሰዎችን አስከሬን፣ ባለሞያዎች በመመርመር ላይ ናቸው፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት፣ ሻካሆላ በተባለው ደን ውስጥ፣ ከመቶ በላይ አስከሬኖች የጅምላ መቃብር ተገኝቷል፡፡

ጥቂት ሰዎች ከነሕይወታቸው ቢገኙም፣ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ እስከ አሁን ከተገኙት አስከሬኖች ውስጥ የሚበዙት ሕፃናት መኾናቸው ታውቋል፡፡

የቀድሞው የታክሲ ሾፌር የነበረው የቤተ ክርስቲያኑ መሪ ፖል ማከንዚ ንቴንጌ፣ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለ ሲኾን፣ ከተያዘበት ጊዜ አንሥቶ፣ ምግብ እና ውኃ ለመቅመስ ፈቃደኛ አልኾነም፡፡

የሟቾቹን ዘመዶች ለመለየት የዘረ መል ምርመራ በመደረግ ላይ መኾኑ ታውቋል፡፡

በአካባቢው፣ ወደ 300 የሚኾኑ ሰዎች ደብዛቸው እንደጠፋ ሲነገር መቆየቱን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG