በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኬንያታን ድጋሚ ማሸነፍ አፀና


ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 16 በድጋሚ የተደረገውን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት አፀና። በዚህም ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ያሸነፉትን ምርጫ አፅድቋል።

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 16 በድጋሚ የተደረገውን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት አፀና። በዚህም ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ያሸነፉትን ምርጫ አፅድቋል።

ጥቅምት 27 በ3 ግለሰቦች ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሄደው ክሥ መዝገብ የኬንያን ድጋሚ ማሸነፍን እንዲሁም የምርጫውን ተዓማኒነት ውድቅ ለማድረግ የቀረበ ሲሆን፥ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማራጋ “የቀረበው ክስ የምርጫውን ውጤት የሚያሽር አይደለም” ሲሉ ውድቅ አድርጎታል።

ባለፈዉ ጥቅምት 27/2010 ዓ.ም ነበር ሦስት የኬንያ ዜጎች በድጋሚ ስለተደረገው የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አግባቢነት ለኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት። ግለሰቦቹ የሲቪል ማኅበረሠብ ተወካዮች ሲሆኑ ያቀረቡትን ክስ በሁለት መዝገብ የቀረበ ቢሆንም ችሎቱ ግን አንድ መዝገብ ላይ አዋህዶ አይቷቸዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኬንያታን ድጋሚ ማሸነፍ አፀና
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:45 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG