በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ በጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የገደሉ ተወሰነባቸው


ኬንያ ውስጥ ከአራት ዓመታት በፊት በጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ የሚበዙት ተማሪዎች የሆኑ አንድ መቶ አርባ ስምንት ሰዎች የገደሉ አክራሪ እስላማዊ ታጣቂዎችን በመርዳት የተከሰሱ ሦስት ወንዶች በኬንያ ፍ/ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቷቸዋል።

ሞሃመድ አብዲ አቢካር ሃሰን አደን ሃሰን እና ራሺድ ቻርልስ ምቤሬሴሮ በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ የቅጣት ውሳኔ ይሰጣቸዋል ያሉት ዳኛው አራተኛው ተከሳሽ ከጥፋቱ ነፃ ተብሉዋል።

የሶማሊያው ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን የአልሸባብ ታጣቂዎች የጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ግቢን ወርረው በርካታ ተማሪዎች መግደላቸው ይታወሳል ታጣቂዎቹም ተገድለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG