በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያው ፕሬዝደንት ካቢኔያቸውን በተኑ


ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ
ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ

በኬንያ ታቅዶ የነበረውን የታክስ ጭማሪ እና የመንግስትን ደካማ አስተዳደር አስመልክቶ ለሣምታት የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ዛሬ ሐሙስ ካቢኔያቸውን በትነዋል።

አዲስና ውጤታማ ያሉትን መንግስት እንደሚያቋቁሙ ሩቶ አስታውቀዋል።

ዛሬ በቴሌቪዥን ቀርበው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ሩቶ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉንም አሰናብተው፣ የሚኒስቴር መሥሪያቤቶቹም በቋሚ ፀሃፊዎቻቸው እንደሚመሩ አስታውቀዋል።

የሕዝቡን ድምፅ ካደመጡ በኋላ ውስኔውን መውሰዳቸን ያስታወቁት ፕሬዝደንቱ፣ ሰፊ መሠረት ያለውን መንግስት እንደሚያቋቁሙ ተናግረዋል።

በኬንያ ለሣምንታት ሲካሄድ በነበረው ተቃውሞ ከ30 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በታክስ ጭማሪ ዕቅድ ላይ የጀመረው ተቃውሞ ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ ወደመጠየቅ ተሸጋግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG