በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤል-አዴ ጥቃት ዓመቱን ደፈነ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሶማሊያ ውስጥ ግዳጅ ላይ በነበሩ የኬንያ ወታደሮች ላይ አልሸባብ ድንገተኛ አደጋ ጥሎ ቁጥራቸው የበዛ ወታደሮችን ከገደለ ልክ አንድ ዓመት ሆነ፡፡

በዚያች ቀን የሚወድዷቸውን ላጡ ወይም የጠፉ ወገኖቻቸው፣ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው የት እንደሚገኙ ገና እየፈለጉ ላሉ ዕለቱ የተለየ ነው፡፡

ጥር ሰባት ሁለት ሺኽ ስምንት ዓ.ም። የሶማሊያው የኹከትና የሽብር ቡድን አል-ሻባብ እዚያው ሶማሊያ ጌዶ ክፍለ-ሃገር ውስጥ ኤል-አዴ ውስጥ በሠፈረው የኬንያ የግዳጅ ሠራዊት መደብ ላይ ድንገተኛ አደጋ ጣለ።

ያንን ጥቃት አል-ሻባብ እራሱ በቪድዮ ቀርፆ ለፕሮፓጋንዳ ተግባሩ አውሎታል።

በዚያ ጥቃት ከመቶ በላይ ኬንያዊያን ወታደሮችን መግደሉን አል-ሻባብ አስታውቋል። በርግጥ የደረሰው ጉዳት ከዚያም በላይ መሆኑን የሚናገሩ ሌሎች ምንጮችም አሉ።

ያኔውኑ ታዲያ የጥቃቱ ወሬ እንደተሰማ በዜናው በብዙ የተደናገጠችው ናንሲ ንጄሪ የባሏን ሁኔታ ለመስማት ስልክ ደወለች - ወደ ሶማሊያ ...

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኤል-አዴ ጥቃት ዓመቱን ደፈነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

XS
SM
MD
LG