በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ በኡጋንዳዊው አትሌት ሞት የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አዋለች


ኢጋንዳዊ አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት
ኢጋንዳዊ አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት

ከኬንያ ኤዶሬት ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ፣ መኪና ውስጥ ተወግቶ ተገድሎ ከተገኘው ኢጋንዳዊ አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት ሞት ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ።

የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ እስጢፋኖስ ኦካል ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት ሁለቱም ተጠርጣሪዎች በ30ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወንዶች ሲሆኑ "ህብረተሰቡን በማሸበር የታወቁ ወንጀለኞች ናቸው" ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹ የታሰሩት ከኤልዶሬት አቅራቢያ መሆኑን ያመለከቱት ኦካል፣ ከግለሰቦቹ አንዱ፣ ፖሊስ ኪፕላጋትን ለመግደል ጥቅም ላይ ውሏል ብሎ ካመነው ቢላዋ ጋር መያዙን ገልፀዋል።

የረጅም ርቀት ሯጭ የሆነው ትውልደ ኬንያዊው ኪፕላጋት በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ የሚታወቅ ሲሆን እ.አ.አ በ2008፣ በ2012 እና በ2016 የተካሄዱ የበጋ ኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ኡጋንዳን ወክሎ ተሳትፏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG