በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረትና ኬንያ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ


ፎቶ ፋይል፦ የአበባ ምርት በኬንያ
ፎቶ ፋይል፦ የአበባ ምርት በኬንያ

የአውሮፓ ሕብረትና ኬንያ ዛሬ ናይሮቢ ላይ የንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል። ከአፍሪካ ጋር ጥልቀት ያለው የኢኮኖሚ ግኑኝነት ለምትሻው አውሮፓ ትልቅ ስኬት ነው ተብሏል።

ስምምነቱ ተግባራዊ ሲሆን አንድ አምስተኛውን የውጪ ንግድ ከአውሮፓ ጋር ለምታከናውነው ኬንያ ከታሪፍ ነጻ የሆነ የንግድ ዕድል የሰጣታል ተብሏል።

ተወዳጅ የሆነው ሻይ ቅጠሏ እና ቡናን የመሰሉ የግብርና ምርቶች እንዲሁም 70 በመቶ የሚሆነውን የአበባ ሽያጭ በስምምነቱ እንደሚካተቱ ታውቋል።

ኬንያ ገበያዋን ቀስ በቀስ ክፍት እንደምታደርግ እና አንዳንድ ሸቀጥችን ግን ስምምነቱ እንደማይጨምር የአውሮፓ ኅብረት ባለስልጣናት ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG