ለኹለት ሳምንታት የዘለቀ የተቃውሞ ሰልፍ የተካሔደባት ኬኒያ፣ በአኹኑ ወቅት መረጋጋት እየታየባት ነው።
ሰልፉን የጠሩት ተቃዋሚዎች እና የአገሪቱ መንግሥት፣ ለንግግር ዕድል ለመስጠት የወሰኑ ቢኾንም፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የተቃውሞ ሰልፎቹ አንዱ ምክንያት የኾነውን የኑሮ ውድነት፣ አስተዳደራቸው ለማስተካከል ያቀደበትን መንገድ አላሳወቁም።
የቪኦኤዋ ማሪያማ ዲያሎ፣ ከናይሮቢ ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡