በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለወራት የታገቱ ሠራተኞች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገለጹ


ለወራት የታገቱ ሠራተኞች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:30 0:00

ለወራት የታገቱ ሠራተኞች የት እንዳሉ አይታወቅም እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገለፁ

ከሦስት ወራት በፊት የታገቱት፣ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና ሦስት ባልደረቦቻቸው ደብዛቸው በመጥፋቱ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

ሠራተኞቹ በፋኖ ታጣቂዎች መታገታቸውንና የማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቀው እንደነበር የገለጹት ቤተሰቦቻቸው፣ እስከ አሁን ድምፃቸውን ሰምተው እንደማያውቁ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ፣ ስለ እገታው መረጃ እንደደረሰው ጠቅሶ፣ ክትትል መጀመሩን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

የታገቱ ሰዎችን በተመለከተ፣ ከአማራ ክልል እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ይኹንና ከዚህ ቀደም እገታው መፈጸሙን ያረጋገጡት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብደላ አሕመድ፣ አባ ገዳዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ለማስለቀቅ እየጣሩ መኾኑን እንደሚያውቁም ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG