በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ


አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ብሬት ካቫኖ ለውሳኔ የሚቀርብልኝን ማንኛውንም ጉዳይ በከፍተኛ አብሮትና በሀቅ እዳኛለሁ ማለታቸው ተሰማ።

አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛብሬትካቫኖ ለውሳኔ የሚቀርብልኝን ማንኛውንም ጉዳይ በከፍተኛ አብሮትና በሀቅ እዳኛለሁ ማለታቸው ተሰማ።

በወሲብ ቅሌት ተከሰው የነበሩት ካቫኖ ከብዙ ውዝግብ በኋላ ነው ትናንት፣ ዛሬ ማክሰኞ የዳኝነት ወንበራቸውን ከመያዛቸው አስቀድሞ፣ የመጨረሻውን ቃለ መሓላ በኃይት ሃውስ የፈፀሙት።

“ሁሉም የአሜሪካ ሕዝብ ነፃና ገለልተኛ ዳኛ እንደምሆን እምነቱን ሊያሳድርብኝ ይችላል” ሲሉም ተናግረዋል።

አሁን በሥራ ላይ የሚገኙት ስምንቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች፣ የካቫኖን ሹመት በጥንቃቄ ሲከታተሉ የነበሩ በርካታ ሪፖብሊካኖችና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ነው፣ በጡረታ የተገለሉት ዳኛ አንቶኔ ኬኔዲ ቃለ መሓላውን ያስፈፀሙት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG