በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሬት ካቫኑ ላይ የተጀመረው የወሲብ ጥቃት ምርምራ ጉዳይ

የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ምርመራ ቢሮ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አባልነት በታጩት ብሬት ካቫኑ ላይ የጀመረው የወሲብ ጥቃት ምርምራ በወጣትነታቸው ጊዜ ኃይለኛ የአልኮል መጠጥ ጠጭ ነበሩ ወደሚለው ክስ ሰፍቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ምርመራ ቢሮ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አባልነት በታጩት ብሬት ካቫኑ ላይ የጀመረው የወሲብ ጥቃት ምርምራ በወጣትነታቸው ጊዜ ኃይለኛ የአልኮል መጠጥ ጠጭ ነበሩ ወደሚለው ክስ ሰፍቷል።

ዶ/ር ክርስቲን ብሌዚ ፎርድ እአአ በ1982 ሁለቱም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እያሉ “ካቫኖ የወሲብ ጥቃት ፈጽመውብኛል” በሚል ለህግ መወሰኛ ምክር ቤት የፍርድ ኮሚቴ አባላት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ካቫኖ በበኩላቸው “አላደርግኩም” በሚል የማስተባባያ ቃላቸውን ለኮሚቴው አስምተዋል። ከኃይለኛ ጠጪነታቸው የተነሳ፣ ስካሩ ከበረደላቸው በኋላ ያደረጉትን አያውቁም ነበር የሚለውንም ክደዋል።

ይሁንና ተማሪዎች እያሉ ጓደኛቸው የነበሩ ቻድ ሉዲንግተን ኃይለኛ ጠጪ እንዳነበሩና በሚጠጡበት ወቅት ንዴታማና ኃይል ተጠቃሚ እንደነበሩ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG