በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሳቫ በሰሜን ኢትዮጵያ


አቶ ኪሮስ ዳኘው
አቶ ኪሮስ ዳኘው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የካሳቫ ሌላ መጠርያ ስሙ ቦዬ ይባላል፡፡ ካሳቫ የሥራ ሥር ውጤት ሲሆን አበቃቀሉ እንደ ቡና እንጨት ረጃጅም ዘንጎች አሉት፡፡

ካሳቫ በምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች የተስፋፋ እጅግ ተወዳጅ ምግብ ነው፡፡ ይህ ተክል መሠረቱ ደቡብ አሜሪካ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመርያ የገባው ዋዱ በሚል ምኅፃር ይታወቅ በነበረው የወላይታ የልማት መርኃግብር ከናይጀርያ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ካሳቫ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም በወላይታ፣ ጎፋ እና አርባ ምንጭ በጣም ይታወቃል፡፡ እንዲሁም በኢሉባቦር፣ በወለጋ፣ በጋምቤላ እና በጅማ ኣከባቢዎችም በብዛት ይገኛል፡፡

ባሁኑ ጊዜ ካሳቫን በሰሜን የኢትዮጵያ አከባቢዎችም ለማስለመድ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት ባልደረባችን ግርማይ ገብሩ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ካሳቫን እያባዙና እያስተዋወቁ የሚገኙትን አቶ ኪሮስ ዳኘውን አነጋግሯል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG