በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንደራሴ ኬረን ባስ በኢትዮጵያ ጉዳይ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኬረን
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኬረን

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኬረን ባስ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ይፈጸማሉ የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የጭካኔ አድራጎቶች በእጅጉ እንዳሳሰቧቸው ገለጹ።

በሪፖርቶች መሰረት በክልሉ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል ጭቅጭቁ ተጋግሎ ባስከተለው ግጭት ሳቢያ ብዙ በሺህዎች በሚቆጠሩ ሲቪሎች ላይ ግድያ፤ አስገድዶ መድፈር ወይም ሌላ አካላዊ ጥቃት ተፈጽሟል ብለዋል የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባልዋ ኬረን ባስ።

በሀገሪቱ ብሄረሰብን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ተባብሷል ያሉት ኬረን ባስ ሰዎች ያለፍርድ ይገደላሉ፤ ወሲባዊ ጥቃት ይፈጸማል፣ ንብረት ይዘረፋል፣ የጅምላ ግድያ ይፈጸማል ብለዋል። ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ረድዔት ተደራሽነቱም መደነቃቀፉ እንደቀጠለ ነው ሲሉ አክለዋል።

ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት መነጋገራቸውን የገለጹት የምክር ቤት አባሏ፣ ግጭቶቹበአስቸኳይ እንዲገቱ እና ተፈጽመዋል በተባሉ ድርጊቶች ዙሪያ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲከፈት አጥብቄ አሳስቤያቸዋለሁ ብለዋል። የህወሓት ሃይሎችና የኢትዮጵያ መንግሥት ሃይሎች ግጭቶቹን በአስቸኳይ አቁመውም ብሄራዊ ውይይት መከፈት አለበት ሲሉ ያሳሰቡት ኬረን ባስ አጣዳፊ ርምጃዎች ካልተወሰዱ ቀውሱ እየተባባሰ ይሄዳል ሲሉ ተናግረዋል።

ከሌሎች የምክር ቤት ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆናቸውንም ነው አክለው ያስታወቁት፥ የሚያቀርቡት ውሳኔ በሃገሪቱ ብሄር እና ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች እና የንብረት ማውደም ተግባር እየተፈጸመ መሆኑን ከግንዛቤ አስገብቶ አድራጎቶቹን የሚያወግዝ ይሆናል ሲሉ ነው የዘረዘሩት።

በጸጥታ ሃይሎች በሰላምዊ ተቃውሚዎች ላይ ከልክ ያለፈ ሃይል መጠቀምን የጋዜጠኞች እና የሰላማዊ ተቃዋሚዎች እስርን እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ባሉ ግለሰቦች እና ቡድኖች በኩል በሚሰራጭ የጥላቻ ንግግር እና የሃሰት መረጃ ምክንያት የሚቀጣጠለውን የጎሳ እና የፖለቲካ ሁለት የሚያወግዝ ውሳኔ እናቀርባለን ብለዋል።

XS
SM
MD
LG