በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ አርብቶ ዐደሮች፣ በድርቅ ምክንያት ችግር ላይ እንደኾኑ ተናግረዋል።
ከፈንታሌ ተራራ አቅራቢያ በተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተፈናቀሉ ያወሱት አርብቶ ዐደሮቹ፣ አኹን ደግሞ በተጠለሉባቸው አካባቢዎች ድርቅ መታየት በመጀመሩ የቁም እንስሶቻቸው እየሞቱባቸው እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
የምሥራቅ ሸዋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ የአደጋ ስጋት እና አመራር ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ መንግሥት ከገባሬ ሠናይ ድርጅቶች ጋራ በመቀናጀት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
መድረክ / ፎረም