በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጦር አዛዦች አደንዛዥ እፅንና ሽብርተኛነትን ለመዋጋት ካቡል ጉባዔ ተቀምጠዋል

የዩናይትድ ስቴትስንና የኔቶ የጦር አዛዦችን ጨምሮ፣ የአፍጋኒስታን አጎራባችና ክልላዊ ሀገሮች ወታደራዊ አዛዦች፣ አደንዛዥ እፅንና ሽብርተኛነትን መዋጋት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመወያየት፣ ዛሬ ማክሰኞ ካቡል ውስጥ ጉባዔ ተቀምጠዋል።

የዩናይትድ ስቴትስንና የኔቶ የጦር አዛዦችን ጨምሮ፣ የአፍጋኒስታን አጎራባችና ክልላዊ ሀገሮች ወታደራዊ አዛዦች፣ አደንዛዥ እፅንና ሽብርተኛነትን መዋጋት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመወያየት፣ ዛሬ ማክሰኞ ካቡል ውስጥ ጉባዔ ተቀምጠዋል።

የአፍጋኒስታን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይዳወላተ ዋዚሪ በሰጡት ቃል፣ ጉባዔው ያነጣጠረው፣ እነዚህ ሁለት ፈተናዎች፣ የአደንዛዥ እፀ ንግድና ሽብርተኛነት ለመጋፈጥ የጋር ጥረት ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ ለመቀየስ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዚህ የአንድ ቀን ጉባዔ ላይ የተካፈሉ ልዑካን፣ በሰላምና በመረጋጋት ላይ ትብብር ለማድረግ መስማማታቸው ታውቋል።

የፓኪስታን ጦር ኃይሎች አዛዥ፣ ጄኔራል ቃማረ ጃቭደ ባጃዋም በዚህ ጉባዔ የተካፈሉ ሲሆን፣ ሀገራቸው ለታሊባን አባላት ከለላ ትሰጣለች በሚል፣ ከአፍጋኒስታንና ከዩናይትድ ሰቴትስ ባለሥልጣናት፣ ነቀፋ ተሰንዝሮባቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG