በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባለፉት ሦስት ዓመታት ተቃውሞ ሰልፍ ለመበተን በሚውሉ መሣሪያዎች 199 ሺ ሰዎች ተጎድተዋል


ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝና ኬሚካል ሲጠቀም፤ ፖርትላንድ፣ ኦሪገን 09/5/2020
ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝና ኬሚካል ሲጠቀም፤ ፖርትላንድ፣ ኦሪገን 09/5/2020

በመላው ዓለም ከእአአ 2015 ወዲህ 119 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በአስለቃሽ ጋዝና በኬሚካል ሲጎዱ፣ 2 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ገዳይ ባልሆነ ተተኳሽ መሣሪያ መጎዳታቸውን ትናንት የወጣ አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ሐኪሞች ለሰብዓዊ መብት እና የሲቪል ነጻነት ድርጅቶች ዓለም አቀፍ ትስስር የተሰኙት ተቋሞች ባወጡት ሪፖርት እንዳስታወቁት ጥናቱ እስከአሁን ከተደረጉና ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን የሚውሉ መሣሪያዎችን በተመለከተ ከወጡ ጥናቶች ሁሉን አቀፍና ሰፊ ጥናት ነው ብለዋል።

ሰልፈኞችን ለመቆጣጠር የሚውሉት መሣሪያዎች ኃይላቸው እየጨመረ መሆኑንና፣ ከሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ላይ አስለቃሽ ጋዝ መተኮስ አንዱ ዘዴ እየሆነ መምጣቱን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

ለጥናቱ የተሰበሰቡት መረጃዎች በአብዛኛው ተጎድተው ድንገተኛ ክፍል ከሚመጡ ሰዎች መሰብሰቡንና ሃኪሞችና የሆስፒታል ሠራተኞች መረጃውን በመሰብሰብ ረገድ እንደተባበሩ ሪፖርቱ ገልጿል።

የጎማ ጥይትና እንደ አስለቃሽ ጋዝ የመሰሉ በጅምላ የሚተኮሱ መሣሪያዎች እንዲታገዱ ጥናት አድራጊዎቹ ጥሪ አድርገዋል፡፡

XS
SM
MD
LG