በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃንተር ባይደን ላይ የተመሰረተውን ክስ የሚመለከቱ ዳኞች ምርጫ ዛሬ ይጀመራል


ሃንተር ባይደን ሰኞ፣ ግንቦት 26፣ 2016 በዊልሚንግተን፣ ዴል በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት ሲደርሱ።. (AP Photo/Matt Slocum) © Provided by The Associated Press
ሃንተር ባይደን ሰኞ፣ ግንቦት 26፣ 2016 በዊልሚንግተን፣ ዴል በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት ሲደርሱ።. (AP Photo/Matt Slocum) © Provided by The Associated Press

በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ልጅ ሃንተር ባይደን ላይ በፌደራል ደረጃ የተመሰረተውንና ከህገ ወጥ የመሳሪያ ግዥ ጉዳይ ጋር የተያያዘውን ክስ የሚመለከቱ ከህዝብ የተወጣጡ ዳኞችን የመምረጡ ሂደት ዛሬ ሰኞ ይጀምራል፡

ጉዳዩ የሚታየው ሃንተር ባይደን ቀደም ሲል ከዓቃብያነ-ሕግ ጋር ያደረጉት ድርድር መፋለሱን ተከትሎ ነው፡፡

ስምምነቱ ባይፋለስ ኖሮ እኤአ የ2024 ምርጫ በተቃረበ ጊዜ የመጣውን ይህን ክስ ማስወገድ ይቻል እንደነበር ተነግሯል፡፡

የሳምንቱን እረፍት ጊዜያቸውን ከአባታቸው ጋር በደለዌር ያሳለፉት ሃንተር ባይደን የተከሰሱት በሶስት የወንጀል ዓይነቶች ነው፡፡

ከዚህ ውስጥ በአደገኛ እጽ ሱስ መያዛቸውን በገለጹበት እኤአ በ2018 በፈደራል ደረጃ ህጋዊ ፈቃድ ላለው የመሳሪያ ሻጭ የሱስ ተጠቂ አለመሆናቸውን በመግለጽ ዋሽተዋል፣ ያልተፈቀደላቸውን መሳሪያ ግዥ በመፈጸም ለ11 ቀናት ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የመሳሪያ ባለቤት ሆነዋል የሚለው ይገኝበታል፡፡

ባይደን አግባብና ፍትሃዊ ባልሆነ መንግድ የፍትህ ሚኒስቴር ኢላማ መደረጋቸውን በመግለጽ ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ የተመሰረተባቸውን ክስ ክደዋል፡፡

ሃንተር ባይደን ሪፐብሊካኖች የፕሬዚዳንቱ ልጅ በመሆናቸው ልዩ አያያዝ ተደርጎላቸዋል ሲሉ ቀደም ሲል የተፋለሰውን ስምምንነት ከተቃወሙ በኋላ ጥፋተኛ አይደለሁም ብለዋል፡፡

የችሎቱ ጉዳይ የተሰማው እኤአ የ2024 ለሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ዶናልድ ትረምፕ በኒው ዮርክ ከተማ በ34 ወንጀሎች የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ጥቂት ቀናት በኋላ ነው፡፡

ከዚህኛው ጋር ባልተያያዘ መልኩ ሃንተር ባይደን 1.4 ሚሊዮን ዶላር ግብር አልከፈሉም በሚል በመጭው መስከረም በካሊፎርኒያ ከችሎት ፊት እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡ ይህኛውም ክስ ከዓቃብያነ-ሕግ ጋር አስቀድሞ ተደርጎ የነበረውና ያልተሳካው ስምምነት አካል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG