ዋሽንግተን ዲሲ —
ወደ 8 ሺሕ የሚጠጉ ስደተኞች በአስከፊ ሁኔታ እንደሚኖሩበት በሚነገረው በዚህ የስደተኛ ሰፈር ከኢትዮጵያ፣ከኤርትራ እና ከአፍጋኒስታን የተሰደዱ ስደተኞች ይገኙበታል።
ከኢትዮጵያ የሚሆኑትን በአስከፊ ሁኔታ የሚኖሩትን ስደተኞች ወደ ሌሎች የስደተኞች ሰፈሮች የማዛወሩ ሂደት አንድ ሳምንት ያህል ሊወስድ ይችላል።
ፍልሰተኞቹ በፈረንሳይ ዙርያ በሚገኙ የስደተኞች ሰፈሮች እንዲሰፍሩ ይደረጋል። ጥገኝነት የመጠየቅ እድልም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ይሁንና አንዳንዶቹ ስደተኞች በእንግሊሽ ቻነል በኩል ወደ ብሪታንያ መዝለቅ ስለሚፋልጉ ወደተባሉት ሰፈሮች አንሄድም ሊሉ ይችልሉ የሚል ስጋት አለ።