በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
በአማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸው ተገለጸ፤ የክልሉ ምክር ቤት የዳኞች ከለላ ዐዋጅን አጸደቀ

በአማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸው ተገለጸ፤ የክልሉ ምክር ቤት የዳኞች ከለላ ዐዋጅን አጸደቀ


ፎቶ ፋይል፦ ባህር ዳር
ፎቶ ፋይል፦ ባህር ዳር

በአማራ ክልል፣ ባለፉት ስድስት ወራት 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸውን፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለም አንተ አግደው፣ ሰሞኑን በተካሔደው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የደኅንነት እና የጸጥታ ስጋት እንዲሁም የክፍያ ማነስ በመንፈቅ ዓመቱ በርካታ ዳኞች ከሥራ መልቀቅ ምክንያት እንደኾነ አስረድተዋል።

28 የወረዳ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች አገልግሎት መቋረጡንም ፕሬዝዳንቱ አክለው ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በመንፈቅ ዓመቱ 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸው ተገለጸ፤ የክልሉ ምክር ቤት የዳኞች ከለላ ዐዋጅን አጸደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:33 0:00

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ሁለት የክልሉ ዳኞች፦ የሞያ ነጻነት ማጣት፣ የደመወዝ ማነስና የደኅንነት ስጋት ሥራቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቃቸው ገፊ ምክንያቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር ተወካይ ሓላፊ አቶ ብርሃኑ አሳሳ፣ ለዳኞች የሥራ መልቀቅ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት የተጠቀሰውን ምክንያት አረጋግጠው፣ የዐዋጁ መጽደቅ ማኅበሩ በተለያየ ጊዜ ሲያነሣቸው የነበሩ ችግሮችን ይቀንሳል፤ ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት፣ ለዳኞች ከለላ እና ጥበቃ ለመስጠት፣ የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ ዐዋጅን አጽድቋል።

ዐዲሱ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ ዐዋጁን አስመልክቶ በኮሚሽኑ የፌስቡክ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ “የዳኝነት ነጻነት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር መሠረት በመኾኑ፣ የዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ ማግኘቱ፦ በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ወሳኝ ነው፤” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG