በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትራምፕ አስተዳደር ለፍልሰተኞች የተሰጠ የከለላ ፈቃድ እንዳያቆም ጊዚያዊ ትዕዛዝ ሰጠ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ዳኛ የትራምፕ አስተዳደር 300,000 ለሚሆኑ ፍልሰተኞች የተሰጠውን የከለላ ፈቃድ እንዳያቆም ጊዚያዊ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከሄይቲ፣ ከሱዳን፣ ከኒካራግዋና ከኤል ሳልቫዶር ለመጡ ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ለመኖርና ለመሥራት የሚያስችላቸው የከለላ ፈቃድ ተስጥቷል።

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ዳኛ የትራምፕ አስተዳደር 300,000 ለሚሆኑ ፍልሰተኞች የተሰጠውን የከለላ ፈቃድ እንዳያቆም ጊዚያዊ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከሄይቲ፣ ከሱዳን፣ ከኒካራግዋና ከኤል ሳልቫዶር ለመጡ ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ለመኖርና ለመሥራት የሚያስችላቸው የከለላ ፈቃድ ተስጥቷል።

የአሜሪካ መንግሥት ወደ ሀገራቸው ቢመልሱ አደጋ ይገጥማቸዋል ለሚላቸው የውጭ ሀገር ተወላጆች ወይም ደግሞ የተፈጥሮ ቀውስን በመሳሰሉት ችግሮች ምክንያት መንግስሥት የተመለሱትን ሊረዳ በማይችልበት ሁኔታ ጊዚያዊ ከለላ ሊሰጣቸው ይችላል።

የጊዚያዊው ከለላ መብት ከተነስ ግን በዛ ጥላ ሥር የነበሩት ሰዎች ከሀገሪቱ ሊባረሩ ይችላሉ።

በካሊፎርኒያ የዩናይትድ ስቴትስ ወረዳ ዳኛ ኤድዋርድ ቼን ታድያ ትላንት ትዕዛዙን ባስተላለፉበት ወቅት የከለላ መብት ያላቸው የውጭ ሀገር ሰዎችና ልጆቻቸው ከለላውን ቢነፈጉ ለከባድ ችግር ይዳረጋሉ ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG