በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ነጋሽ ገብረማርያም - ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ፀሐፌ-ተውኔት፣ አስተማሪ


ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም
ጋዜጠኛና ደራሲ ነጋሽ ገብረማርያም

ሰኞ፣ ሐምሌ 10/2009 ዓ.ም. ያረፉት የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ የአቶ ነጋሽ ገብረማርያም አስከሬን ሥርዓተ-ቀብር ዛሬ ተፈፀመ። አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ያረፉት ባጋጠቸው የኩላሊት መታወክ ሕክምና እየተከታተሉ ሳሉ ነበር።

አዲስ ዘመን ጋዜጣ ወደ አምስት ቀን ዕለታዊ ዕትምነት እንዲያድግ የረዱት አቶ ነጋሽ ገበረማሪያም የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ሆነው ከሐምሌ 1953 ዓ.ም. አንስቶ ለአራት ዓመታት አገልግለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅም ሆነዋል፡፡

አቶ ነጋሽ ገብረማሪያም ያረፉት በ93 ዓመት ዕድሜያቸው ነው፡፡

አስከሬናቸው ዛሬ ከቀትር በኋላ በስህሊተ-ምህረት ቤተክርስቲያን መካነ-መቃብር አርፏል፡፡

የሕልፈታቸውን ምክንያትና ሕይወታቸውን አስመልክቶ ልጃቸው ወ/ት ስንዱ ነጋሽ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን አጭር ቃለ ምልልስ የያዘውን ዘገባ ከድምፅ ፋይሉ ያዳምጡ፡፡

ነጋሽ ገብረማርያም - ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ፀሐፌ-ተውኔት፣ አስተማሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:32 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG