ዋሺንግተን ዲሲ —
የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላ የካቢኔ አባል የነበሩትን ኡማር ራዛዝን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሾመዋል። በሀገሪቱ የሚካሄደው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ግን ቀጥሏል።
ትላንት ከሥልጣን የወረዱትን ሀኒ ሙልኪን ይተካሉ። ሙልኪ የቁጠባ ዕርምጃ እንዲካሄድ ሲገፉ ቆይተዋል።
በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች መንግሥት የዋጋ ማናርና ግብር የመጨመሩን ዕቅድ እንዲያቆም በመጠየቅ ከትላንት ማታ ጀመረው እስከ ዛሬ ንጋት ከሥልጣን ወደ ወረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት አምርተዋል። በዋጋ መናርና በግብር መጨመር በተለይም የሚጎዱት የመካከለኛው መድብና በድኅነት የሚኖረው ሕዝብ ናቸው የሚል ዕምነት አለ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ