በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዮርዳኖስ ጠ/ሚ ኡመር ራዛዝ አጨቃጫቂ የግብር ዕቅድን ለማንሳት አቀዱ


የዮርዳኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡመር ራዛዝ
የዮርዳኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡመር ራዛዝ

የዮርዳኖሱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡመር ራዛዝ ለአንድ ሳምንት ያህል የዘለቀውን ተቃውሞ ያስነሳውን አጨቃጫቂ የግብር እቅድን እንደሚቀለብሱ ዛሬ አስታውቀዋል።

የዮርዳኖሱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡመር ራዛዝ ለአንድ ሳምንት ያህል የዘለቀውን ተቃውሞ ያስነሳውን አጨቃጫቂ የግብር እቅድን እንደሚቀለብሱ ዛሬ አስታውቀዋል።

ራዛዝ ከሀገሪቱ ምክር ቤት ጋር ከተነጋገሩ በኋላ “የቀረጡን ዕቅድ ለማንሳት ሥምምነት ተደርጓል” ሲሉ አማን በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባዔ ገልፀዋል።

ንጉስ አብዱላ የካቢኔ ሚኒስትር የነበሩትን ራዛዝ ባለፈው ማክሰኞ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾሙት ሐኒ ሙልኪ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሰናበቱ በኋላ ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የቀየሱት የቁጠባ ዕርምጃ ከፍተኛ ተቃውሞ አስንስቷል።

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ተወላጆች በቁጣ ሰልፍ በመውጣት መንግሥት የቁጠባ ዕርምጃውን እንዲተው ጠይቀዋል። ዓለምቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባደረገው ጫና ምክንያት የቀረበው ፖሊሲ የኑሮ ደረጃውን እንደሸረሸረ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG