በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዮርዳኖስ የሥለላ አገልግሎት ጥቃቶችን ማክሸፈን ገለፀ

የዮርዳኖስ የሥለላ አገልግሎት እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን በሀገሪቱ ለማካሄድ ያቀደውን ትልቅ ተከትታይ ጥቃቶችን እንዳከሸፈ የመንግሥት የዜና አገልግሎት ዛሬ ዘግቧል።

የዮርዳኖስ የሥለላ አገልግሎት እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን በሀገሪቱ ለማካሄድ ያቀደውን ትልቅ ተከትታይ ጥቃቶችን እንዳከሸፈ የመንግሥት የዜና አገልግሎት ዛሬ ዘግቧል።

“ፔትራ” የተባለው የዜና አገልግሎት በገለፀው መሰረት ሀገሪቱ አሥራ ሰባት ሰዎችን አስራለች። በለዘብተኛ የሀይማኖት መሪዎች፣ በፀጥታ ተቋማትና በሌሎች ቦታዎች ላይ ጥቃት ለማካሂድ ካቀደ ህዋስ ላይ መሣርያዎችን ይዛለች።

ቡድኑ የጥቃቱን ፅቅድ ለማንቀሳቀስ ሲል ባንኮችን የመዝረፍና መኪናዎችን የመሥራቅ ዓላማ እንደነበረው፣ ከአካባቢው ገበያ ከገዛቸው ቁሶች ፈንጂዎችን እንደሠራም ተገልጿል።

በዩናይትድ ስቴትስ የተመራው የጥምረት ኃይል በአሸባሪው ቡድን ላይ በሚያካሄደው ውጊያ ዮርዳኖስ ዋና የአሜሪካ አጋር ነች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG