በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አራት ሃገሮች በሱዳን ጉዳይ መግለጫ አወጡ


 አብደላ ሀምዶክ
አብደላ ሀምዶክ

ሳዑዲ አረብያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ዩናትይትድ ስቴትስና እንግሊዝ፣ በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል እኤአ ህዳር 21/2021 በተደረሰበት ሥምምነት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ወደ ሥልጣን መመለስን አስመልክቶ ዛሬ ባወጡት መግለጫቸው አድንቀዋል፡፡

በተወሰደው እምርጃ የተበረታቱ መሆኑን ገልጸው ሥምምነቱን የፈረሙ ወገኖች ቃላቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በመጠየቅ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡

እኤአ በ2019 ህገ መንግሥቱን መሰረት አድርጎ በተደረሰበት ሥምምነት የተወሰደው እምርጃ የሱዳንን የፖለቲካ ቀውስ መፍትሄ የሚያስገኝ የመጀመሪያው ምርእራፍ መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል፡፡

የፖለቲካ ተቃዋሚዎች መፈታታት፣ ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ የሚያጣራ ኮሚቴ መቋቋሙ፣ እንዲሁምየ አስችኳይ ጊዜ ዐዋጁ በቅርብ ጊዜ እንዲነሳ መታሰቡን ሁሉ እንደ አበረታች እምርጃ እንወስዳለን ብሏል መግለጫው፡፡

መግለጫው እንዲሁም በሠራዊቱና በሲቪሉ መካከል ሥምምነትን ለመፍጠር በሚደረገው ውይይት በጥምረቱ ወቅት ተሳታፊ የነበሩትን የፖለቲካ ኃይሎች የማሳተፍ አስፈላጊነትን አበክረን እንገልጻለን ሲል አሳስቧል፡፡

እኤአ በ2023 መጨረሻና በ2024 መጀመሪያ ላይ ይደረጋል ለተባለው ምርጫ ሂደቱን የሚያመልከት ፍኖተ ካርታ ከወዲሁ ታትሞ መውጣቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን ሲልም የሃገራቱ መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሃገራቱ መግለጫ ለሱዳን ህዝብ ያለንን የግልና የተናጥል ድጋፍ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን ሲል አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG