በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የ5 ሚሊዮን ዶላር የ“ሞ - ኢብራሂም” ተሸላሚ ሆኑ

ፎቶ ፋይል፡- የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ
ፎቶ ፋይል፡- የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ

ቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የ5 ሚሊዮን ዶላር የ“ሞ - ኢብራሂም” ተሸላሚ ሆኑ።

ቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የ5 ሚሊዮን ዶላር የ“ሞ - ኢብራሂም” ተሸላሚ ሆኑ።

የ”ሞ-ኢብራሂም” ሽልማት፣ በአፍሪካ የመልካም አስተዳደር እውቅና ላገኙ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።

ሚስ ጆንሰን ሰርሊፍ፣ እአአ ከ1944 ወዲህ ላይቤሪያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽግግር የታየበትን ርክክብ ባለፈው ወር ማድረጋቸው አይዘነጋም።

ላይቤሪያን ለሁለት የስድስት ዓመታት የሥልጣን ዘመን የመሩት ጆንሰን ሰርሊፍ፤ የኖቤል ሰላም ሎሬት በመሆን የመጀመሪያዋ ተመራጭ አፍሪካዊት መሪ ሴት ተሸላሚ ሆነዋል።

በላይቤሪያ የቀድሞዋ የ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በሰጡት ምስክርነት፣ “ሰርሊፍ ሥልጣናቸውን ያስረከቡት፣ ሀገሪቱን በመሪነት ሲረከቡ ከነበረችበት በተሻለ ደረጃ ላይ አድርሰው ነው” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG