በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጃንሰን ኤንድ ጃንሰን የመድሃኒት ኩባኒያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሙከራውን ለጊዜው አቋረጠ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ግዙፉ የዩናይትድ ስቴትሱ የመድሃኒት ኩባኒያ ጃንሰን ኤንድ ጃንሰን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሙከራውን ለጊዜው አቋርጧል።

ምክንያቱም በክትባቱ ላይ በተጀመረው የኋለኛ ዙር ብዛት ያላቸው ሰዎች ያሳተፈ ሙከራ የተሳተፈ አንድ በጎ ፈቃደኛ በመታመሙ መሆኑን ኩባኒያው አስታውቋል።

ግለሰቡ የታመመው ማንነቱ ለጊዜው በውል ያልታወቀ ህመም እንደሆ ነው ያመለከተው። የጃንሰን ኤንድ ጃንሰኑ በአንድ ጊዜ የሚሰጥ የኮቪድ ክትባት ዩናይትድ ስቴትስን እና ባራዚል እንዲሁም ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ ሃገሮች ስድሳ ሺህ በጎ ፈቃደኞችን ያሳተፈ የመጨረሻ ዙር ሙከራ ሂደት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG