በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሂደት


ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለው ግዙፉ የዩናይትድ ስቴትስ የመድሃኒት ኩባኒያ የቀመመውን በአንድ ጊዜ የሚሰጥ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት የመጨረሻ ምዕራፍ በሰው ላይ ሙከራ ሂደት ጀምሯል።

የኩባኒያው የሳይንሳዊ ጉዳይች ክፍል ዋና ባለሥልጣን ስካት ስቶፍልስ ትናንትና ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኙ 215 ስፍራዎች እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ደቡብ አፍሪካ፣ አርጀንቲናና ብራዚልን ጨምሮ በተለያዩ ሃገሮች ክትባቱ በ60,000 በጎ ፈቃደኞች ላይ እየተሞከረ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትርምፕ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ፍለጋ ርምጃ ያስደሰታቸው መሆኑን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። የሃገሪቱን የክትባት ማረጋገጫ ፈቃድ ሰጪ ባለሥልጣን መስሪያ ቤት ኤፍዲኤ በአስቸኳይ መንቀሳቀስ አለበት ሲሉም አሳስበዋል።

ከአሁን ቀደም በሞዴርና፥ አስትራ ዜኔካና በፋይዘርና የጀርመኑ ባዮቴንክ ኩባኒያ ህብረት የመጨረሻ ዙር ሙከራ ላይ ከደረሱት ጋር የጆንሰን ኤንድ ጆንሰኑ አራተኛ ነው።

XS
SM
MD
LG