በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጆን ቦልተን መጽሐፍ መታተም እንደሚችል ፍርድ ቤት ወሰነ


ጆን ቦልተን
ጆን ቦልተን

የፍትህ ሚኒስቴር ባስቸኳይ እንዲታገድ አቤቱታ ቢያስገባም የፌደሬል ፍርድ ቤት ዳኛውየቀድሞ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን መጽሐፋቸውን ማሳተም ይችላሉ ሲሉ ዛሬ ውሳኔ ሰጥተዋል

የፍትህ ሚኒስቴር መጽሐፉ ታትሞ ከወጣ የመንግስት ሚስጥራዊ መረጃዎች ውጭ ሊወጡ ይችላሉ በማለት ህትመቱ እንዲታገድ ጠይቋል

የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ሮይስ ላምበርት በሰጡት ውሳኔ በሺዎች የሚቆጠር የመፅሐፉ ቅጂ ታትሞ ወደመጽሐፍት መደብሮች እየተላከ በመሆኑ ህትመቱ መቀጠል ይችላል ብለዋል

በዓለም ዙሪያ በተለይም በዜና ድርጅቶች እጅ ብዙ መቶ ሺህ ቅጂዎች ተሰራጭተው ባለበት ሁኒታ ህትመቱን ማስቆሙ የሚቀይረው ነገር አይኖርም ሲሉም ዳኛው አስረድተዋል

በዋይት ሃውስ ባሳለፉት የአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕን የውጭ ፖሊሲ አወሳሰን በተመለከተ የሚነቅፉበት የጆን ቦልተን መጽሐፍ የፊታችን ማክሰኞ ገበያ ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል

XS
SM
MD
LG