ከታህሳስ 3-7 /2013 ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ለሚወጡ ወጣቶች የተዘጋጀ የሥራ ፈላጊና አሠሪ ቀጣሪዎችን የሚያገናኝ “የሥራ አውደ ርዕይ” በአዲስ አበባ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገው የሥራ አውደ ርዕይ ("Virtual Career Expo") በኮቪድ 19 ምክንያት የተካሄደው በድረ ገጽ ሲሆን ከ114 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶችና ከ4ሺ በላይ ምሩቃን ተካፋዮች የተሳተፉበት መሆኑን አዘጋጆቹ ይናገራሉ፡፡
ተመራቂዎችንና ሥራ ቀጣሪ ድርጅቶችን የሚያገናኘው የደረጃ ዳት ካም ፕሮግራም ድሬክተር ወ/ት ሲሃም አየለ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት፣ ድርጅታቸው ከመንግሥት የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን፣ ከዩኒቨርስቲዎች፣ እንደ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ከመሳሰሉ ለጋሽና ከሌሎች ቀጣሪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር፣ ተማሪዎቹ ከመመረቃቸው በፊት፣ ልዩ የብቃት ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
እስካሁን ወደ 6ሺ ተመራቂ ተማሪዎችን ከአሠሪዎች ጋር በማገናኘት ለሥራ ብቁ ያደረጓቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በየክልሉ ዩኒቨርስቲዎች ስላሉት የሥራና የሙያ ማበልጸጊያ ተቋማት የሥራ እንቅስቃሴም አካፍለውናል፡፡
ምናሴ ሙላው እና ብሌን ደስታ የተባሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የቅድስት ማርያም ኮሌጅ ተማሪዎችም ከድርጅቱ ስላገኙት ሥልጠና እና ድጋፍ እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሥራ አጥነት ችግር የሚናገሩት አላቸው፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡