በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭት


የሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:14 0:00

የሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭት

በአማራ ክልል ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የመጡ ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች፣ በአጎራባቾቹ የሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም እና ቀወት ወረዳዎች ሥር በሚተዳደሩ የገጠር አካባቢዎች፣ “ግድያ፣ የንብረት ጉዳት እና ዘረፋ ፈጽመዋል፤” ሲሉ ተጎጅ ነን ያሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፉርሲ ወረዳዎች የሚኖሩ አስተያየት ሰጭዎች በአንጻሩ፣ ግጭቱ የተቀሰቀሰው፣ “የፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሞ ብሔረሰብ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት በመሰንዘራቸው ነው፤” ብለዋል፡፡

ኩሪ ቢሪ፣ የለን፣ ዋጮ፣ ሞላሌ እና ነጌሶ በተባሉ የኤፍራታ ግድም እና ቀወት ወረዳዎች ሥር ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ፣ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት፣ ንጹሐን ሰዎች መገደላቸውን፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የደረሱ ሰብሎች መቃጠላቸውን፣ የአካባቢው የመረጃ ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል፡፡ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ከገጠር ቀበሌዎቹ እንደሸሹም፣ እኒሁ የመረጃ ምንጮች አመልክተዋል፡፡

የአርጡማ ፉርሲ ነዋሪ የኾኑ አንድ አስተያየት ሰጪም፣ “ችግሩ መቼ እንደሚያገረሽ ስለማይታወቅ አካባቢ ላይ ውጥረት ነግሧል፤” ብለዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታ ግድም ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ፣ ችግሩ መከሠቱን አረጋግጠው የጉዳቱን መጠን ለማወቅ ጥረት እየተደረገ እንደኾነ አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ዋና አስተዳዳሪው አልብስ አደፍራሽ፣ ጠንካራ ሕግ የማስከበር ሥራ እና ተጠያቂነት ካልሰፈነ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋም ኾነ ከአርጡማ ፉርሲ ወረዳዎች አስተዳደር፣ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG