በድጋሚ የታደሰ
ጂል ባይደን በቀዳማዊ እመቤትነታቸው ዘመን የመጀመሪያ የሆነውን የአፍሪካ ጎብኝት ዛሬ ረቡዕ በናሚቢያ ጀምረዋል፡፡
ጂል ባይደን በአፍሪካ ጎብኝታቸው ሴቶችን በማብቃት፣ በሕጻናት ጉዳዮች እንዲሁም በአንዳንድ የአህጉሪቱ ክፍል እየታየ ያለውን የምግብ ዋስትና እጦት በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ታደርጋሉ፡፡
“የቀዳማዊ እመቤቷ ጉብኝት ባለፈው ታህሳስ በተደረገው የዩኤስ አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለአፍሪካ ሙሉ ትኩረት ለመስጠት የገቡት ቃል አካል ነው” ሲሉ በብሄራዊ ጸጥታው ምክር ቤት ከፍተኛ ሃላፊ የሆኑት ጀድ ደቨርሞንት ለዜና ሰዎች ተናግረዋል፡፡
ጂል ባይደን በናሚቢያ ያደረጉት ጉብኝት አገሪቱ ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት እአአ 1990 ወዲህ በአሜሪካ ቀዳማዊ እመቤት የተደረገ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
ቀዳማዊ እመቤቷ በአፍሪካ ጉብኝታቸው በሕጻናትና ሴቶች ጉዳይ ላይ ከማተኮራቸው በተጨማሪ፣ በኬንያ በሚያደርጉት ጉብኝት ምሥራቅ አፍሪካን አስጨንቆ ስላለው የምግብ ዋስትና እጦት ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
ጂል ባይደን ከዚህ ቀደም እንደ ሁለተኛ እመቤት አፍሪካን 5 ግዜ ጎብኝተዋል፡፡