በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂል ባይደን ኮቪድ ያዛቸው


የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ጂል ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ጂል ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ጂል ባይደን ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸውንና ከትናንት ምሽት ጀምሮ ጉንፋን መሰል ስሜት እየተሰማቸው መሆኑን ዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት አስታወቀ።

ጂል ባይደን ቀላል የኮቪድ-19 ስለሚስተዋልባቸው ፓክስሎቪድ የሚባለው መድኃኒት እንደታዘዘላቸው የቤተ መንግሥቱ ቃል አቀባይ ካሪን ዣን-ፒየር ገልፀዋል።

ቀዳሚት እመቤቲቱ ትናንት፤ ሰኞ በቤት ውስጥ የሚደረገውን ሁለት ጊዜ ምርምራ አድርገው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ቢያሳይም በኋላ ግን በተካሄደላቸው ጠለቅ ያለ የላብራቶሪ ምርመራ ለኮቪድ-19 መጋለጣቸው ተረጋግጧል።

የ71 ዓመቷ ጂል ባይደን ሁለት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትና ሁለት ማጠናከሪያዎችን መውሰዳቸው ታውቋል።

ባለቤታቸው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም ከአሥር ቀናት በፊት ለኮቪድ-19 ተጋልጠው ህክምና ላይ ከቆዩ በኋላ አሁን ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ወደ ሥራቸው መመለሳቸው ይታወቃል።

በሃገሪቱ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ) መመሪያ መሠረት ሚስ ባይደን ለመጭዎቹ አምስት ቀናት ከማንም ተግልለው ህክምናቸውን እንደሚከታተሉ ዋይት ሃውስ አክሎ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG