በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂል ባይደን አውሮፓን እየጎበኙ ነው፣ ከዩክሬን ስደተኞችም ጋር ይገናኛሉ


በአውሮፓ ጉብኘት በማድረግ ላይ የሚገኙት የዩናዩትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን
በአውሮፓ ጉብኘት በማድረግ ላይ የሚገኙት የዩናዩትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን

በአውሮፓ ጉብኘት በማድረግ ላይ የሚገኙት የዩናዩትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን፣ የሩሲያን ወረራ ተክትሎ በሩማንያ የተሰማሩ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችን አመስግነዋል፡፡

የአራት ቀን ጉብኝታቸውን ዛሬ አርብ የጀመሩት ባይደን በሩሲያ ወረራ የደረሰውን የስደተኞች ቀውስ በስፍራው ተገኝተው ይመለከታሉ ተብሏል፡፡

ዋይት ኃውስ እንዳስታወቀው ባይደን መጭውን የእናቶች ቀን በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው የስሎቫኪያ መንደር ከሚገኙ ተፈናቃይ ቤተሰቦች ጋር ያሳልፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡ ቀዳማይ እመቤቲቱ ወደ ዩክሬን ዘልቀው ስለመግባታቸው ጽ/ቤታቸው ምንም ነገር ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡

የሩሲያ ወረራን በመሸሽ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩክሬናውያንን እንደ ስሎቫኪያና ሩማንያ ወደ መሳሰሉ አጎራባች አገሮች መሰደዳቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG