በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጂግጂጋ ግጭት


ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ውጥረት ላይ በሰነበተችው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂግጂጋ ማምሻውን የመከላከያ ሠራዊት በመግባቱ ከተማው በመረጋጋት ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ።

ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ውጥረት ላይ በሰነበተችው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂግጂጋ ማምሻውን የመከላከያ ሠራዊት በመግባቱ ከተማው በመረጋጋት ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ።

በሌላ በኩል የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ሞሀሙድ ኦማር በይበልጥ በሚታወቁበት ስማቸው አብዲ ኢሌ በአዲስ አመራር መተካታቸውን የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ።

በጂግጂጋ የተከተሰተውን ግጭት ተከተሎ በድሬደዋ ከተማ ገንደ-ገራዳ በተባለው አካባቢ በትላንት እና በዛሬው ዕለት በተከሰቱ ግጭቶች ቁጥራቸው 14 የሚደርሱ ዜጎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በሌላ ተያያዥ ዜና “በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ በከተማዋ የሚኖሩ ዜጎችን ሰብአዊ መብት አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ በፍጥነት ሊቆም ይገባዋል” ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከጂግጂጋው ብጥብጥና ሁከት ጋር በተያያዘ “ደርሷል” ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክቷል። በከተማዋ በዜጎች ደሕንነትና በንብረት ላይ የደረሰው ውድመት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውም ሲልም ኮምሽኑ ገልጧል።

በሕዝብ ላይ የደረሰውንም ሆነን በንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለጊዜው መግለጽ እንደሚያዳግተው የተናገሩት የኮምሽኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዲሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ፤ አያይዘውም “በወንጀሉ ተጠያቂ የሆኑትን ወገኖች ማነት ጨምሮ ተጨማሪ ምርመራና መረጃዎችን ማደራጀት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮሚሽነር ጀማል መሐመድ በበኩላቸው በክልሉ ጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ ሱቆች ላይ ዘረፋ መፈጸሙንና ቤተክርስቲያን መቃጠሉን ገልጸዋል። ዜጎች ለደህነነታቸው መስጋታቸውን “አንዳንዶችም ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰ ነው፤” ብለዋል።

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አክለውም፤ሁከትና ብጥብጡን ተከትሎ የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባልታወቁ ሰዎች መቃጠሉንና በጽህፈት ቤቱ ያሉ የምርመራ ሰነዶች መቃጠላቸውንና መዘረፋቸውንም አመልክተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG