በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጅግጅጋ የሚገኘው "ኦጋዴን" ተብሎ የሚጠራው ማረሚያ ቤት ተዘጋ

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውና በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንፁሀን ዜጎች የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥቃት ይፈፀምበት ነበር የተባለውን "ኦጋዴን" ተብሎ የሚጠራው ማዕከላዊ ማረሚያ ቤት መዘጋቱን የሀገር ውስጥ የዜና ማሰራጫዎች ዘገቡ፡፡

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውና በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንፁሀን ዜጎች የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥቃት ይፈፀምበት ነበር የተባለውን "ኦጋዴን" ተብሎ የሚጠራው ማዕከላዊ ማረሚያ ቤት መዘጋቱን የሀገር ውስጥ የዜና ማሰራጫዎች ዘገቡ፡፡

የክልሉ መንግሥት ካቢኔ በአካሄደው ስብሰባ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በሺህዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንፁሀን ዜጎች የሚታጎሩበትና በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ይፈፀምበት የነበረ ነው” በሚል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውን ማዕከላዊ ማረሚያ ቤት እንዲዘጋ ወስኗል፡፡

በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ምሁራን እንዲሁም ለረጅም ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመዘዋወር በክልሉ የሚፈፀሙትን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችን ሲቃወሙና ሲታገሉ የቆዩ ሰዎች በተገኙበት ማረሚያ ቤቱ በይፋ ተዘግቷል፡፡

የተዘጋው የጅግጅጋ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ሕጉን መሰረት በማድረግ እንደሚለቀቁም የክልሉ መንግሥት መግለጫን ዋቢ በማድረግ የወጣው ዘገባ አመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG